ፈቲያ መሀመድ በአለም ዓቀፍ የወይዘሮ ቱሪዝም ንግስት የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ ትሳተፋለች!!

ፈቲያ መሀመድ በኩዋላላንፑር ማሌዥያ በሚካሄደው የአለም ዓቀፍ የወይዘሮ ቱሪዝም ንግስት የቁንጅና ውድድር (Mrs Tourism Queen International Pageant) ኢትዮጵያን ወክላ ትሳተፋለች። የኢትዮጵያ የቱሪዝም አምባሳደር የሆነችው ፈቲያ መሀመድ በውድድሩ ስትሳተፍ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ልማት ታስተዋውቃለች፣ በሃገራት መካከል ወዳጅነት እንዲኖርና ለባህል ልውውጥ መጎልበትም የበኩሏን  ትወጣለች።

ውድድሩን ያዘጋጀው በዓለም አቀፍ የቁንጅናና ፋሽን ውድድሮች እውቅና ያለው ዓለም አቀፉ የወይዘሮ ቱሪዝም ንግስት ድርጅት ነው። ውድድሩ በአይነቱ አዲስ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹም ቀደም ሲል ሃገራቸውን ወክለው በቁንጅና ውድድር ማዕረግ ያላቸውና አሁን ላይ ትዳር መስርተውና ልጆች ወልደው ራሳቸውን የጠበቁ ወይዛዝርት የሚሳተፉበት ነው።

በውድድሩ አሸናፊ የምትሆነው ወይዘሮ የምትመረጠው ባላት ተፈጥሯዊ ውበት ብቻ ሳይሆን በምታሳየው ልዩ ችሎታ/ክህሎትና የሀገሯን ባህልና ቱሪዝም በማስተዋወቅ ረገድ በምታሳየው የራስ መተማመንም ጭምር ነው።

አለም አቀፍ ልምድ ያላቸው ዳኞች የሚዳኙትን ይህን ውድድር በተለይ ነሃሴ 24 የመጨረሻው ውድድር ሲካሄድ የተለያዩ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዝግጅቱን በቀጥታ ያስተላልፉታል።

በዚህ ውድድር ላይ ተመልካቾች ድምፅ እንዲሰጡ የማይፈቀድላቸው ቢሆንም የፈቲያ መሃመድን ዌብሳይትን (www.fetihyamohammed.com) እና የፌስቡክ (https://www.facebook.com/fetihyamo) አካውንትን ላይክ፣ ኮሜንትና ሼር በማድረግ ወዳጆቿና አድናቂዎቿ ድጋፋቸውን እንዲሰጧት እንጋብዛለን።

50 ሀገራት ይሳተፉበታል ተብሎ  በሚጠበቀው በዚህ ውድድር ላይ መሳተፉ ብቻ ለሀገር ገፅታ ትልቅ ዋጋ የሚኖረው ሲሆን፥ በውድድሩ የምታሸንፈው ወይዘሮ ደግሞ  ከአለም አቀፉ የቱሪዝም ድርጅትና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመሆን ሀገሯን ለማስተዋወቅ የሚያስችላት ሰፊ እድል ይፈጥርላታል።

ኢትዮጵያን ወክላ የምትሳተፈው ፊቲያ መሃመድ ከአሜሪካ ከጃፓን፣ አውስትራሊያ፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቡልጋሪያ፣ ኢስቶንያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ህንድ፣ ካዛኪስታን፣ ኬንያ፣ ማሌዥያ፣ ሜክሲኮ፣ ሞንጎሊያ፣ ማይናማር፣ ኔፓል፣ ኒውዝላንድ፣ ፊሊጵንስ፣ ፖርቹጋል፣ ሮማንያ፣ ሩስያ፣ ሲንጋፖር፣ ደ/ኮርያ፣ ስሪላንካ፣ ስዊድን፣ ታይላንድ፣ ኔዘርላንድ እና ቬትናምን የሚወክሉ ወይዛዝርት ይሳተፉበታል።

ለፈቲያ መሀመድ መልካም ዕድል እንመኛለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *