ዓለምአቀፍ የወይዘሮ የቱሪዝም ንግስት ውድደር

ዓለምአቀፍ የወይዘሮ የቱሪዝም ንግስት ውድደር ( Mrs. Tourism Queen International Pageant) ቀደም ሲል በቁንጅና ውድድርና በሞዴሊንግ ሞያ ውስጥ ያሳለፉና ትዳር መስርተውና ልጆች ወልደው ራሳቸውን ጠብቀው የቆዩ ባለትዳር ሴቶችን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሰብስቦ በአይነቱ ልዩ የሆነና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ ውድድር ነው፡፡ 

ውድድሩ ያገቡና በሞዴሊንግ ልምድ ያላቸው ሴቶችን ክህሎት፣ ውበትና ስኬት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹም ከውበታቸው ባለፈ ስለ ትዳርና ቤተሰብ ያላቸውን እምነትና አስተሳሰብ ያብራራሉ፣ የአገራቸውን በጎ ዕሴቶች ያስተዋውቃሉ እንዲሁም ወቅታዊ ስለሆኑ ጉዳዮች ያላቸውን ሀሳብ ያካፍላሉ፡፡ 

በዘመናዊው ዓለም ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ሰላላቸው ስፍራ፣ ስለ ሴቶች መብት እና ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ስለማብቃት ሙያዊ የሆነ ውይይት ይካሄዳል፡፡ 

ዓለምአቀፍ የወይዘሮ ቱሪዝም ንግስት ውድድር ከዓለም ዙሪያ በተውጣጡ ተሳታፊዎችና ታዳሚዎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ቅርርብ የሚፈጥር፣ የባህል ልውውጥን የሚያጎለብት፣ ወንድማማችነትና ጓደኝነትን የሚያበለፅግና በልዑካኑ መሀከልም መግባባት እንዲፈጠር ያስችላል፡፡ 

ዓለምአቀፍ የወይዘሮ ቱሪዝም ንግስት ውድደር ሌላም ዓላማ አለው፤ የአገራትን የቱሪዝም ልማት እንዲጎለብት ማሰቻል፣ በአገራት መሃከልም መቀራረብን ማሳደግና የባህል ልውውጥ እንዲከሰት ማድረግ፡፡ 

በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር የሚሳተፉ አገራትም የንግድ ምልክቶቻቸውን፣ የቱሪስት መዳረሻዎቻቸውን፣ ለጎብኚዎች የሚጠቅሙ ምርቶቻቸውን፣ የፋሽንና የቅንጦት ሸቀጦችን ሁሉ በዚህ መድረክ የሚያስተዋውቁበት ዕድል ያገኛሉ፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *